ብዙ አሉ ሊያገኟት የተጉ
ሳይደርሱባት ተሳልመው የሞቱ
ከሩቅ እያዩያት ጉልበታቸው ካዳ
ጊዜም እረሳቸው ታሪካቸው ጠፋ
ብመለከት ማዶ ከባቢሎን ሆኜ
ብድራቴን ለየሁ ግዞት ተቀምጬ
የኤፍራጢስ ወንዝን መሻገሬ አይቀርም
በባርነት ሀገር ከእንግዲህ አልኖርም
ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን
ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን
ባማረ ቅኝት በሰመረ ዜማ
ስጠራው ሰማኋት ስሜን በመዝሙሯ
"ና!" ብትለኝ በለሆሳስ ድምጿ
ልፈልጋት ወጣው ላቋርጥ በጀልባ
ብመለከት ማዶ ከባቢሎን ሆኜ
ብድራቴን ለየሁ ግዞት ተቀምጬ
የኤፍራጢስ ወንዝን መሻገሬ አይቀርም
በባርነት ሀገር ከእንግዲህ አልኖርም
ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን
ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን
ማሲንቆዬን ከሰቀልኩበት
ላውርድ እና ቅኔን ልቀኝበት
እያለቀስኩ አስብሻለው
አልረሳሽም ቃል ገብቻለው
ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን
ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን ጽዮን