ድንገት አጥቼሽ
ልቤን አሞኛል
ሳትነግሪኝ ጠፍተሽ
ይሄዉ ውዴ ግራ ገብቶኛል
ንገሪኝ ወዴት ነሽ ስበር እመጣለዉ
ካላየዉ አይንሽን እንዴት እሆናለዉ
አጣው እረፍት አጣው
እረፍት አጣው ጠፍተሽ
የትነሽ ብፈልግሽ
ዙሪያዬን ባይ የለሽ
ሊጀማምረኝ ነው ደግሞ ልትናፍቀኝ
ሊመጣ ትዝታዋ አቅሜን ሊያሳጣኝ
የቀን ቅዠት ሊሆንብኝ
የቀን ቅዠት ሊሆን
የቀን ቅዠት ሊሆንብኝ
የቀን ቅዠት ሊሆን
አይጥመኝ ጨዋታ አንቺ የሌለሽበት
ከኔ እርቋል ደስታ ጠፍተሽ ሄደሽበት
ወይ አይገዙት ፍቅርን በወርቅ አልማዝ
አይቀይሩት በእቃ በእጅ አይያዝ
ዉጪ ዉጪዉን እየቃኘ
ተንከራተተ አይኔ ደጅ እያየ
ትመጫለሽ ብሎ ደግ እየተመኘ
ወዴት ትሆን ብሎ ባሳብ እየዋኘ
አጣው እንቅልፍ አጣው
እንቅልፍ አጣው ጠፍተሽ
የትነሽ ብፈልግሽ
ዙሪያዬን ባይ የለሽ
ሊጀማምረኝ ነው ደግሞ ልትናፍቀኝ
ሊመጣ ትዝታዋ አቅሜን ሊያሳጣኝ
የቀን ቅዠት ሊሆንብኝ
የቀን ቅዠት ሊሆን
የቀን ቅዠት ሊሆንብኝ
የቀን ቅዠት ሊሆን
ሊጀማምረኝ ነው ደግሞ ልትናፍቀኝ
ሊመጣ ትዝታዋ አቅሜን ሊያሳጣኝ
የቀን ቅዠት ሊሆንብኝ
የቀን ቅዠት ሊሆን
የቀን ቅዠት ሊሆንብኝ
የቀን ቅዠት ሊሆን