ስንባዝን ዋልን እታች ላይ እያልን
እምናገኛት መስሎን ስንደክም ኖርን
ስንፈልጋት ከረምን ወዲ ወዲያ እያልን
በዳበሳ ዳከርን ጨለማው ውጦብን
ግድ የለም ያልፋል ብርሃን ይሆናል
የጋረደን ቅርፊት ከዓይናችን ይወድቃል
ያኔ ይገባናል ነፃ መውጣታችን
እውነት እንደፈታን ከእስራታችን
ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን
ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን
በአዙሪት መንገድ የትም ሳንራመድ
ቆሰለ እግራችን ዛለ ጉልበታችን
እራሳችንን ጠላን ይቅር ላለማለት
ሳናውቀው ታሰርን በፀፀት ገመድ
ግድ የለም ያልፋል ብርሃን ይሆናል
የጋረደን ቅርፊት ከዓይናችን ይወድቃል
ያኔ ይገባናል ነፃ መውጣታችን
እውነት እንደፈታን ከእስራታችን
ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን
ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን
በመውጣጥ መውረድ እየተደናቀፍን
ዓይናችን ታውሮ ሳናውቀው ወደቅን
ብርሃን ያገኘናል ጨለማ አይውጠንም
ነፃ ያወጣናል ከራሳችን እስር
ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን
ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን ብርሃን ይሁን