የእምባው ጠብታ ከአይኑ ሲወጣ ይወርዳል ከጉንጩ አልፎ እስከ ከመሬት
በሲቃ ሲጣራ ድምፁ ባይወጣም ይሰማል ስቃዩ በስትንፋሱ ምሬት
ደረቱን ቢመታ ልብን ቢደበድብ
ምቱ በርትቶበት ይቀደዋል ያን ልብስ
ማቁ ቢታይበት ከውስጥ የለበሰው
ሳይራሩ ገለጡት ምስጢሩን ተሳልቀው
ምንጮች ሁሉ ይሄዳሉ ወደወንዝ
ምንጭ ሆኖ ዓይኑ እምባው ሆኖ ወንዝ
ምንጮች ሁሉ ይሄዳሉ ወደወንዝ
ምንጭ ሆኖ ዓይኑ እምባው ሆኖ ወንዝ
ይቀል ይሆናል የውሃው ሙሌት
ይራመድ ይሆናል ማግሥት ሲመጣ በደረቅ መሬት
ግን እስከዚያው ድረስ ያ ቀን ስኪመጣ
ሲጠብቅ ይኖራል ከወንዙ ዳርቻ
ደረቱን ቢመታ ልብን ቢደበድብ
ምቱ በርትቶበት ይቀደዋል ያን ልብስ
ማቁ ቢታይበት ከውስጥ የለበሰው
ሳይራሩ ገለጡት ምስጢሩን ተሳልቀው
ምንጮች ሁሉ ይሄዳሉ ወደወንዝ
ምንጭ ሆኖ ዓይኑ እምባው ሆኖ ወንዝ
ምንጮች ሁሉ ይሄዳሉ ወደወንዝ
ምንጭ ሆኖ ዓይኑ እምባው ሆኖ ወንዝ
እንደ ወንዝ ቢሆን እምባ ጥልቅ ቢሆን ሀዘን
እንደተሰበረ አይቀርም እንዳዘነ መንፈስ
መመለስ ይሆናል መንገድ ለጠፋበት
ምንጩ ይደርቅ እና ይቀላል ያ ወንዝ
ምንጮች ሁሉ ይሄዳሉ ወደወንዝ
ምንጭ ሆኖ ዓይኑ እምባው ሆኖ ወንዝ
ምንጮች ሁሉ ይሄዳሉ ወደወንዝ
ምንጭ ሆኖ ዓይኑ እምባው ሆኖ ወንዝ