ብቻህን ከምትሄድ ብዙ ሆነኸ ተጏዝ
ያንተን ተሸክመኽ የሌላውንም ያዝ
ከደግነት መንገድ ፊትህን አታዙር
በማማ ላይ ሆነክ በሰዎች ልብ ኑር
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
ሰዎች ሁሉ ልብ ካለ ልግስና
የሚሰጡ እጆች መና አይቀሩምና
ከእጅ ስለጠፋው ከቶ አትማረር
ያጣኸውን ሁሉ እንደሰጠኽ ቁጠር
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
መቆም ስትጀምር የወደቀን አንሳ
ወደፊት ስትሄድ ጀርባህን አትርሳ
እቺ አልቦ አለም ሙሉ እምትሆነው
ያከማቸ ሁሉ ያለውን ሲሰጥ ነው
መቆም ስትጀምር የወደቀን አንሳ
ወደፊት ስትሄድ ጀርባህን አትርሳ
እቺ አልቦ አለም ሙሉ እምትሆነው
ያከማቸ ሁሉ ያለውን ሲሰጥ ነው
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ
ሰብስቦ ከሚኖር የሚሰጥ ቀምቶ
ሳይሻል አይቀርም ከሚኖር ሰስቶ
መልካም ባይባልም በሁሉ እይታ
ካንድ ሰው ይሻላል የብዙዎች ደስታ