ይታየኛል ጎህ ሲቀድ ሲያልፍ ጨለማው
የማለዳው ብርሀን ቀኑን ሲወርሰው
አሻግሬ አያለው አሁን ካለንበት
ተስፋን ስንይዘው ሲሆነን ሕይወት
ቢደክምም ያሁን ልፋት
ቢመስልም ነገ ጥፋት
እውነት ብትደበዝዝ
ባትታይ ደምቃ እንዳልማዝ
ከእቅብ ስር ቢሆን ሻማችን
ፍርሀት ቢሸሽግብን
ግን እንነሳለን ያልፋል ሀዘናችን
እያሪኮ ይፈርሳል ስንመጣበት
ውቅያኖሱ ይከፈላል ስንራመድ
ፀሀይ ትቆማለች ካዘዝናት
ለምን ብትል ምድር ፍቅር ሆነን ምክንያት
ይታየኛል ጎህ ሲቀድ ሲያልፍ ጨለማው
የማለዳው ብርሀን ቀኑን ሲወርሰው
አሻግሬ አያለው አሁን ካለንበት
ተስፋን ስንይዘው ሲሆነን ሕይወት
ቢደክምም ያሁን ልፋት
ቢመስልም ነገ ጥፋት
እውነት ብትደበዝዝ
ባትታይ ደምቃ እንዳልማዝ
ከእቅብ ስር ቢሆን ሻማችን
ፍርሀት ቢሸሽግብን
ግን እንነሳለን ያልፋል ሀዘናችን
እያሪኮ ይፈርሳል ስንመጣበት
ውቅያኖሱ ይከፈላል ስንራመድ
ፀሀይ ትቆማለች ካዘዝናት
ለምን ብትል ምድር ፍቅር ሆነን ምክንያት
እያሪኮ ይፈርሳል ስንመጣበት
ውቅያኖሱ ይከፈላል ስንራመድ
ፀሀይ ትቆማለች ካዘዝናት
ለምን ብትል ምድር ፍቅር ሆነን ምክንያት