ለኔ ሰጠኝ መውደድን
ለኔ ሰጠኝ ፍቅርሽን
ለኔ ሰጠኝ መውደድን
ለኔ ሰጠኝ ፍቅርሽን
ለኔ ሰጠኝ
እኔን ብላ የተጎዳች
ፍቅርን ብላ የተሰዋች
ከፊቴ ያለች እየመራች
ችግሬንም እየፈታች
ሁሉን ትታ ከኔጋ ነች
እርግማንም የሌለበት
የተሰራች ምድረገነት
አለምልማኝ ከአፈር ምሬት
ላይጠወልግ የኔም ህይወት
በአለም ላይ ስኖር ሰጥኝ ከሁሉም የሚሻል
የፍቅር ሊቅ አዋቂ ጌጤ ለአንገቴ ኒሻን
ፍቅርሽ መአዛ አለው ከሩቅ ይሸታል እንደጣን
ስጪኝ መዳኒት ነው ለኔ ህመሜን የሚያድን
ከቁጥር አንድ ከፊደል ሀ የመጀመሪያነች
ከልጅነት እስከ እውቀቴ ከኔጋ የፀናች
ፍቅርም ነግሶ ባካላቴ ልቤም እሚመታው
ያሳሰበኝ ህልሜ እራሱ ባንቺ ነው የተፈታው
ጥልቅ ውበታም የሚመረጥ ላአይንም ጎልቶ እሚታይ
ተማርኮ ነው የወሰድሽው አይኔ ሌላ ላያይ
ስወድሽም ከልቤነው የለም ካንቺ በላይ
የፍቅር ልብስ አልብሰሽኝ
በልብሽ ውስጥ አንግሰሽኝ
በደስታ ላይ ደስታን ሰተሽ ደስ እንዲለኝ አደረግሺኝ
አታቅ መቅናት ለኔ ሳቅ ናት
ህይወት ሲጎብጥ ደርሳ ማቅናት
አንቺን እንኮን ለኔ ሰጠኝ
በአለም ላይ ስኖር ሰጥኝ ከሁሉም የሚሻል
የፍቅር ሊቅ አዋቂ ጌጤ ለአንገቴ ኒሻን
ፍቅርሽ መአዛ አለው ከሩቅ ይሸታል እንደጣን
ስጪኝ መዳኒት ነው ለኔ ህመሜን የሚያድን
እኔን ብላ የተጎዳች
ፍቅርን ብላ የተሰዋች
ከፊቴ ያለች እየመራች
ችግሬንም እየፈታች
ሁሉን ትታ ከኔጋ ነች
ፍቅር ለውሳ ሰላሜን
ጪስ አጪሳ እጣኑን
ባዶነቴን የቤቴን
አባረረች ችግሬን
በአለም ላይ ስኖር ሰጥኝ ከሁሉም የሚሻል
የፍቅር ሊቅ አዋቂ ጌጤ መክበሪያየ ኒሻን
ፍቅርሽ መአዛ አለው ከሩቅ ይሸታል እንደጣን
ለኔ መዳኒት ነው ለኔ ህመሜን የሚያድን
በፀሎቴ መሀል መሀል ሁሌም የማስብሽ
ደግ ደጉን ሁሌ ላንቺ ክፉም እንዳይነካሽ
አይኔን ጥርሴ ልቤን ብቻ እሱ ምን ዋጋለው
እኔ ላንቺ ስጋ አይደለም ነብሴን ነው እምሰጠው
ተምሬአለሁ ሁሉን ካንቺ የፍቅርን ቁምነገር
ፍቅር ሰቶ መቀበልን ከፍቶ የፍቅርን በር
አብሮ መኖር ማደግ እና በደስታ መሻገር
ሜዳሊያየ ነሽ ያስጌጥሽኝ
ኒሻኔ ነሽ ያኮራሽኝ
ዝናሬ ነሽ የታጠኩሽ በህይወቴም ያጀገንሺኝ
ከንዳ አጥንት ለኔ ሰራት
የሁሉ እናት ጀግና ሴት ናት
እሳን እንካን ለኔ ሰጠኝ
በአለም ላይ ስኖር ሰጥኝ ከሁሉም የሚሻል
የፍቅር ሊቅ አዋቂ ጌጤ ለአንገቴ ኒሻን
ፍቅርሽ መአዛ አለው ከሩቅ ይሸታል እንደጣን
ፍቱን መዳኒት ነው ለኔ ህመሜን የሚያድን
ለኔ የኔ
ለኔ ሰጠኝ
ለኔ