ሁሌም ደሞ ኑር እንደደላህ
ሰላም ይንገስ በልብህ
ለአንተ አለም ትሁን የፍቅር ደሴት
የሀሴት ጅረት የማይነጥፍባት
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የልቤ ሰው መፅናኛዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የህሊና ጋብቻዬ
የጀምበር ግባት የዶሮ ጩኸት ጓደኛዬ ነህ
ነባሩን ሽረው ባዲስ ሲተኩት >> >>
ጀርባውን ሲሰጥ ትናንት ያመኑት >> >>
እኛ ግን አለን ሳይለየን ወረት
ከእናቱ ልጅ በልጦ ቅናት ልቡን ገዝቶት
ለአቤል ሞት ከሆነ የቃዬል መሰዋዕት
መወለድ ቋንቋ ነው ስም ነው ወንድምነት
ቅዱስ ነው ይበልጣል የእኛስ ጓደኝነት
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የልቤ ሰው መፅናኛዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የህሊና ጋብቻዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የልቤ ሰው መፅናኛዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የህሊና ጋብቻዬ
ጅምሬ ሰምሮ ቁጭቱ እንዲያምር ጓደኛዬ ነህ
ነህና ለኔ የሙሴን በትር >> >>
አንተ መለከት ለስኬት በር >> >>
ሰላም ይብዛ እንደ አምላክ ፍጡር
ከፈጣሪ ሌላ ጣልቃ ሳይገባበት
አንድ ሆነህ እንደ ሺህ በልቤ ሙላበት
ስር ሰዶ ፍቅራችን በእድሜ ተፈትኗል
ልክ እንደ ወይን ጠጅ ሲቆይ ይጣፍጣል
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የልቤ ሰው መፅናኛዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የህሊና ጋብቻዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የልቤ ሰው መፅናኛዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የህሊና ጋብቻዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የልቤ ሰው መፅናኛዬ
ጓደኛዬ ጓደኛዬ
የህሊና ጋብቻዬ