ቃላት ባጣ የውስጤን የልቤን ባይገልጽልኝ
እንዲህ ብዬ እንዲያም ብዬ ደርሶ ቢወጣልኝ
ቃልም የለኝ ለሰራኸው የተራዬን ልበል ይኸው
እንዳረከው ባይመጥንም ከመዘመር ዝም አልልም
ቃላት ባጣ የልቤን የውስጤን ባይገልጽልኝ
እንዲህ ብዬ በፊትህ ብመጣ ቢወጣልኝ
ቃልም የለም ለሰራኸው የተራዬን ልበል ይኸው
እንዳረከው ባይመጥንም ከመዘመር ዝም አልልም
ትላንትናዬን ሳስበው እኮ እንዴት እንዴት ነበረ
ለማለፍ ከብዶ ቢታይም ሞቴን በህይወት ቀየረ
የትላንትናው ደመና እንደጉም ሄደ በነነ
አዲስ ቀን ዛሬ ሆነልኝ ልቤም በኢየሱስ ታመነ
ተቀይሯል አሁን የትላንቱ የለም
የትላንቱ የለም
ቃልኪዳኑን አጥፎ ጌታ ዞር አላለም
ጌታ ዞር አላለም
ተቀይሯል አዎ ዛሬ ምስጋና ነው
ዛሬ ምስጋና ነው
ደግፎ የያዘኝ የጌታ እጅ ነው
የኢየሱስ እጅ ነው
የለም ሃዘን የለም ጭንቀት የለም
የለም በመድኃኔ ዓለም
የለም ሃዘን የለም ጭንቀት የለም
የለም
ቃላት ባጣ የልቤን የውስጤን ባይገልጽልኝ
እንዲህ ብዬ በፊትህ ብመጣ ቢወጣልኝ
ቃልም የለም ለሰራኸው የተራዬን ልበል ይኸው
እንዳረከው ባይመጥንም ከመዘመር ዝም አልልም
ቃላት ባጣ የውስጤን የልቤን ባይገልጽልኝ
እንዲህ ብዬ እንዲያም ብዬ ደርሶ ቢወጣልኝ
ቃልም የለኝ ለሰራኸው የተራዬን ልበል ይኸው
እንዳረከው ባይመጥንም ከመዘመር ዝም አልልም
ሙሉ ለሊቱን ስለፋ
የሚያዝ አንድም ሲጠፋ
ማልዶ ቢነካው መረቤን
ሰርቶት አሳየኝ ነገሬን
ዛሬማ ፈጥኖ ልቤ ነው
ኢየሱስ ሲባል የሚያምነው
ዓምናም ባህሩን ከፍሎታል
ነገም ደግሞ ድሉ የኔ ነው
ተቀይሯል አሁን የትላንቱ የለም
የትላንቱ የለም
ቃልኪዳኑን አጥፎ ጌታ ዞር አላለም
ጌታ ዞር አላለም
ተቀይሯል አዎ ዛሬ ምስጋና ነው
ዛሬ ምስጋና ነው
ደግፎ የያዘኝ የጌታ እጅ ነው
የኢየሱስ እጅ ነው
የለም ሃዘን የለም ጭንቀት የለም
የለም በመድኃኔ ዓለም
የለም ሃዘን የለም ጭንቀት የለም
የለም በመድኃኔ ዓለም