ይፈሳል ወንዝ በመሀል
እኔን ከአንቺ ለይቷል
አፈሩን ሁሉ ወስዶታል
ውሃው ሲጋጭ ይሰማል
ያደርስ ይሆን ወይ የላኩትን ሸማ
ጠልፌው ነበረ በናፍቆቴ ዜማ
ነግሬው ነበረ እንደምዘገይ
ሰምተሽስ ይሆን ወይ ድጡ እንደያዘኝ
ይሄዳል ይሄዳል
ሰምቶ እንዳልሰማ እያየኝ ያልፋል
ወንዝ አይታመንም መች ፍቅር ያውቃል
ላያደርስ መልክቴን አቋርጦ ይፈሳል
ይነፍሳል ነፋስ በመሀል
እኔን ከአንቺ ለይቷል
ቅጠሉን ሁሉ አራግፎታል
ዛፉ ብቻውን ይጮሀል
ያደርስ ይሆን ወይ የላኩትን ሸማ
ጠልፌው ነበረ በናፍቆቴ ዜማ
ነግሬው ነበረ እንደምዘገይ
ሰምተሽስ ይሆን ወይ ድጡ እንደያዘኝ
ይሄዳል ይሄዳል
ሰምቶ እንዳልሰማ እያየኝ ያልፋል
ነፋስ አይታመንም መች ፍቅር ያውቃል
ላያደርስ መልክቴን አቋርጦ ይነፍሳል
ወንዙና ነፋሱ ጥለውኝ ሄዱ
የሚሄዱበትን ሳይናገሩ
እንደው ካየሻቸው ወዳንቺ ከመጡ
መልክተኞች ናቸው አልፈው እንዳይሄዱ
ይሄዳሉ ይሄዳሉ
ሰምተው እንዳልሰማ እያዩኝ ያልፋሉ
ወንዙና ነፋሱ በእኔ ላይ ጨከኑ
ላያደርሱ ፍቅሬን ድንበሩን አለፉ